ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የማህበራዊ አገልግሎት የጤናና ልማት ድርጅት(OSSHD) መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

News
Blog-Image

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የማህበራዊ አገልግሎት የጤናና ልማት ድርጅት(OSSHD) መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ በ“ስትራቴጂካዊ አጋርነት” መግባቢያ ላይ የደረሱት ተቋማቱ፤ የስምምነት ሰነድ የፊርማ ስነ-ስርአቱን ያከናወኑት በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ነው፡፡ በስነ-ስርአቱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገነነ ሩጋ፤ ባንኩ የማህበራዊ አገልግሎት የጤና እና ልማት ድርጅት(OSSHD)ን አላማዎችን ለማሳካት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

የተቋማቱን ተገልጋዮች ህይወት ለማገዝም በ“ስትራቴጂካዊ አጋርነት” መስራቱ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሸለ መልኩ ለውጤት የሚያበቃ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የማህበራዊ አገልግሎት የጤና እና ልማት ድርጅት(OSSHD) ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በቀለ ሰንበቴ በበኩላቸው የባንኩ የረጅም ጊዜ ደንበኞች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የስትራቴጂክ አጋርነት ፊርማው ይህንን ነባር ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡ ሁለቱ ተቋማትም በአብሮነት በ“ትውልድ ነገ” ላይ ለመስራት መስማማታቸውን አድንቀዋል፡፡ *** ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!