ድርጅታችን BftW ከተባለ አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር የፕሮጀክት ስምምነት አከናወነ

News
Blog-Image

ድርጅታችን ከዚህ በፊት ከ BftW ከተባለ አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በአዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ አና ጎንደር ከተሞች የስነተዋልዶ ጤና ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምእራፍ ከ 2019 አኤአ ጀምሮ አስከ ጁን 30/2023 ድረስ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ሁለተኛውን ምእራፍ ድርጅታችን ከግብረሰናይ ድርጅቱ ጋር በተደረገ የጋራ ስምምነት መሰረት ለሚቀጥሉት ሶሰት አመታት የሚቆይ አዲስ የፕሮጀክት ስምምነት አከናውኗል፡፡ በመሆኑም ይህ የኤች አይ ቪ /ኤድስ እና ስነተዋልዶ ጤና ፕሮጀክት ከ ጁላይ 01/2023 ጀምሮ አስከ ጁን 30/2026 ድረስ በአዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ አና ጎንደር ከተሞች ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡